ድነት
ድነት
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:16]
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ [ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23]
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። - [ወደ ሮሜ ሰዎች 6:23]
ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 14:6]
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:12]
ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:3]
እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም። - [ወደ ዕብራውያን 9:22]
እንዲህም አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። - [የማቴዎስ ወንጌል 18:3]
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። - [የዮሐንስ ራእይ 3:20]
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። - [1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:9]
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። - [ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9,10,13]
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። - [ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8,9]
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ - [ወደ ቲቶ 3:5]
እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። - [የሐዋርያት ሥራ 16:31]
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:36]
እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። - [ኛ የዮሐንስ መልእክት 10:28]
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። - [2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17]
ይህን አጭር ጸሎት ከልብ ይጸልዩ
ጌታ ሆይ ሀጢአተኛ እንደሆንኩኝ አውቃለሁ
ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሰራሁትን ሀጢአቴን
ይቅርበለኝ እኔ ን ለማዳን ብለህ ሀጢአ ቴን ሁሉ በመስቀል ላይ ተሸክመህ
እንደሞትክልኝ አምናለሁ
ለእኔ ስትል ባፈሰስክዉ በ ንጹህ ደምህ ሀጢአቴ ን ሁሉ እጠብልኝ
አለምን ሰይጣንን ክፉውን ሁሉ ክጃለሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አንተን መርጫለሁ
ወደልቤ አንድትገባ የህይወ ቴም አዳኝና ጌ ታሁን
ጌታ ስለሆንከኝ ልጅህ ስላደረከኝ አመሰግንሀለሁ
በጌ ታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜ ን።
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17